School of Abigail on Clubhouse

School of Abigail Clubhouse
882 Members
Updated: Mar 12, 2024

Description

ሰላም ቅዱሳን!

እንኳን ወደ አቢጊያ የትምህርት ማዕከል (School of Abigail) በሰላም መጡ::

የስሙ ስያሜ፦
አቢግያ ማለት አብዮት ማለት ሲሆን አብዮት ማለት ደግሞ ሥር ነቀል ለውጥን የሚያመጣ ማለት ነው። ከዚህም ባሻግር ይህን ስም የሰየምንበት ምክንያት፦ ከንጉሥ ዳዊትና አብራው ወደ ኬብሮን ከወጣችው ከንጉሡ ሚስት ከአቢግያ ጋር የተያያዘ ሰፊና ጥልቅ የሆነ አሳብን የያዘ ነው። (ተጨማሪ አሳብ ከፈለጉ ይጠይቁን)

ዓላማው ፦
እውነተኛ በሆነው የክርስቶስ ትምህርት በአማኞች ሕይወት ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥን በማምጣት የመጠራቱን ተስፋ ባለማወቅ ከተያዙበት የናባል ቤት ወይም ሲስተም አላቅቆ ለንጉሡ ሚስት ወደ ሚሆኑበት ብቃት ማምጣትና ፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ ወደሚሆኑበት ወደ ኬብሮን (intimacy) ተራራ በሙሉነት እንዲወጡ ማድረግ።

ሥራችን፦
ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊውን ጉዞ እንድትጓዝ የተጠራች ናት። ካለ መንፈሳዊ ጉዞ መንፋሳዊ እድገት የለም። ስለሆነም ከመንፈስ ቅዱስ የምናገኘው የቃሉ ብርሃን የልጁን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንደሚለውጠን እናምናለን። ከዚህ የተነሳ ከክብር ወደ ክብር የሚያሻግረንን ጽኑና እውነተኛ ፤ የማይናወጥና ዘላለማዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት ለማስተማር በእግዚአብሔር ተልከናል።

ትምህርት
ከዚህ ቀድሞ ላለፉት ሀለት አመታት በzoom ስናጠና የነበረውን የመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን መጽሐፍ በዚህ clubhouse room በአዲስ መልኩ በሰፊው እንደ ጌታ ፈቃድ ጀምረናል:: ኑ! እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ያስቀመጠውን ፀጋ እንድንከፋፈል እና በመጨረሻው ዘመን እግዚአብሔር ሊሰራ ባለው ስራ ሠራዊት ሆኖ ለመሰራት እና ከእርሱ ጋር አብሮ ሰራተኞች ለመሆን እርሱን በመምሰል አብረን ሆነን እንደግ እያልን የከበረ የፍቅር ግብዣችንን በጌታ ፍቅር እናቀርባለን::

መርሃ ግብር
ሰኞ:- የመኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን ትምህርት
[9:00 AM PST 12:00 PM EST 7:00 PM ETHIO]

ሐሙስ:- የጫማ ፈቱ ቤት መፅሃፍ ውይይት
[9:00 AM PST 12:00 PM EST 7:00 PM ETHIO]

አርብ:- የጽዮን አልቃሾች ፀሎት ጊዜ
[6:00 AM PST 9:00 AM EST 4:00 PM ETHIO]

ቅዳሜ:- እውነተኛዋ ቤተ-ክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ ትምህርት እና ውይይት
[9:00 AM PST 12:00 AM EST 7:00 PM ETHIO]

Last 30 Records

Day Members Gain % Gain
March 12, 2024 882 +36 +4.3%
January 22, 2024 846 +31 +3.9%
December 08, 2023 815 +28 +3.6%
October 31, 2023 787 +17 +2.3%
October 01, 2023 770 +40 +5.5%
September 01, 2023 730 +7 +1.0%
August 04, 2023 723 +50 +7.5%

Charts

Some Club Members

More Clubs