በአዳም በመሆናችን በአዳም ያለው ሁሉ የግድ ወደ እኛ ተላልፏል፣ የእኛ ሆኖል። እንደዚሁም በክርስቶስ ስንሆን የክርስቶስ የሆነው ሁሉ በእግዚአብሔር ፀጋ የእኛ ሆኖል።
የቀደመው ፍጥረት በመስቀሉ ተሸሮ አዲስ ፍጥረት የሆነው ሁለተኛው ሰው ከሞት ተነስቶ ወደ ህይወት መጥቷል። በዚህም የቀደመው ማንነታችን ከክርስቶስ መስቀል ጋር ሲያከትም ፣ አዲሱ ማንነታችን ግን ከትንሳኤው ጋር ጀምሯል።
"ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፣ አሮጌው ነገር አልፏልና፣ እነሆ ሁሉ አዲስ ሆኗል ።"
2ኛ ቆሮ 5 ፥ 17
።።።።።።።
" ... ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።"
(2ኛ ቆሮንቶስ 4:5)
።።።።።።።።።።።።።