🕍 עַם יִשְׂרָאֵל חַי
ወልቃይት ጠገዴ ዳንሻና ሁመራ
ስውም ጎደሬ ነዉ መሬቱም አማራ
ዳባት አረዳጄን አጅሬ ጃኖራ
ወልቃይት ጠገዴ ዳንሻና ማይካድራ
ወፍአርግፋ አቀወርቅ ከጀግኖቹ ጎራ
ላይ ሶላ ታች ሶላ ከፍታና ሁመራ
ጎስመዉ ባፈሙዝ ዳኘዉ በከዘራ 💚💛❤️
ማረሻው ምንሽር ማጎልጎያው ጓንዴ
አጨደው በበልጅግ ወቃው በጎራዴ
ያመጸኛው መቅጫ የነጮቹ ዳንዴ
ያባ ደፋር አገር ወልቃይት ጠገዴ 💚💛❤️
ጎንደር ጠገዴ ወልቃይት
የጀግና እናት
ረጋ አጅሬ የባህር አዞ
አይወቀስም እጅ ተይዞ
እጅ ተይዞ ከሚወቀስ
መሞት ይሻላል አፈር መልበስ 💚💛❤️
ይምጣ አጉሐላ ይምጣ አርባያ ይምጣ በለሳ
ጉድብ ሳይሰራ በጠራው ሜዳ እጅ የሚያስነሳ 💚💛❤️
ጥይት ሲያጓራ ኪ,,ል ሲል ካርታ
ሆዱ አይሸበር ልቡ አይፈታ 💚💛❤️
ሃገሬ በለሳ ኸረ መናው ወንዙ
ውሃው ይጣፍጣል ማር እንደ በረዙ 💚💛❤️
እንዴት ነው ሶሮቃ የጀግኖቹ ሃገር
እንዴት ነው ጠገዴ የፋኖዎች ሃገር
በአማራነቱ የማይደራደር
ሲደላው ገበሬ ሲከፋው ወታደር
💚💛❤️
ሀገር እንደ ጎንደር ሰው እንደ ጎንደሬ
ስሙን ጥሪው ጥሪው ይለኛል አስሬ 💚💛❤️
ለጋሼ
"መግደል መሸነፍ ነው"
ብለው የነገሩን
በጅምላ በጅምላ
አርገው ከሚቀብሩን
ምነው ማሸነፍን
ሞተው ቢያስተምሩን?!