Barok Daco on Clubhouse

Updated: Dec 8, 2023
Barok Daco Clubhouse
279 Followers
89 Following
@barok.daco Username

Bio

💚💛❤️ ...🗝

#ከ አይሁድ ጫጫታ ይልቅ ጲላጦስን ሰላም የነሳው የ ክርስቶስ ዝምታ ነው።

#ገጣሚ ቅርብ ከሆነ ማንም እንደ እዝን ንፍሮ ይዘግነዋል። ገጣሚ ግን ሲርቅ ልባሞች ብቻ ይረዱታል። ሚ.አ

"ስነግጥም፣ ቅኔ የጥበብ ሁሉ እናት ናት!" — ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን

ጋሽ ፀጋዬ ይህንን ያለው ለሶስት ብርቱ ምክንያቶች ይመስለኛል።

፩) በቋንቋ ውበት ከስነፅሁፍ ዘርፎች ስነግጥምን የሚወዳደር አንድ እንኳን የለም

፪) ግጥም የሃሳብ ጉልበታም ነው

፫) ግጥም በባህሪው እምቅ ነው። እንደ ቢግ ባንግ ፅንሰሃሳብ ከሆነ ዩኒቨርስ በመጀመሪያ ኢንፋናይት ዴንሲቲ የነበረው ሚጢጢ አካል ነበር። ይህ አካል ከታመቀበት ሲፈነዳ ይህንን ግዙፍ ዩኒቨርስ አስገኘ። ገጣሚውም በጥቂት መስመሮች እምቅ ሃሳብ ያሰፍራል። አንባቢው ጋር ሲደርስ ሚጢጢዎቹ ስንኞች ፈንድተው ግዙፍ ሃሳብ እና ስሜት በተደራሲው እዝነልቦና ይፈጥራሉ። አንድ ግሩም ግጥም ባነበብን ቁጥር ቢግ ባንግ ቲዎሪን እንደገና እየታዘብን ነው!

# ስሙን ያላወኩት እንደፃፈው

.............

ሀይማኖት እንጅ እምነት የላችሁም ..በድን አስከሬናችሁን ልካችሁ የወገን ልብ ትሰብራላችሁ፣ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፣ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፣ባፍ ትጀምራላችሁ በወረት ትተዉታላችሁ፣ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፣ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፣ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፣ የረገጣችሁን ትይዛላችሁ፣ ምኞታችሁ ልክ የለውም፣አምሮታችሁ ብዙ ነው፣ ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል፣ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ ባንዱ ግን አትጠቀሙበትም፣ ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ፣ ሃይማኖት እንጂ ዕምነት የላችሁም፣ ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትፀፀታላችሁ፣ ታማችኋል፣ ከታሪክ ፍቅርና ልማትን ሳይሆን ጥላቻና ልማትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ፣ ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣ ደረታችሁን ነፍታችሁ፣ሳትመርጡ ሁሉና ባደባባይ ትዘሩታላችሁ" ስል ግል ኑሮዓችን የምንኳትን ምስኪኖች ነን፤ አንተ ደግሞ ፍለጋው የማያልቀው የዚህ ትውልድ ናሙና ነህና አምነህ ሂድ ብልህ አትቀበለኝም እንደ ቶማስ በእጅህ ዳሰህ ካላየህ አትረካም፣ የትውልዱ ሕመምም ይህ ነው፣አንተም የዚህ ትውልድ ተጠቂ ምሳሌ ነህና….አንተን ሊያቆምህ የሚችለው የመንገዱ ማለቅ ብቻ ነው፤ ሩቅ መንገደኛ የሚያቆመው አንድም መንገዱ ሲያልቅ አለዚያም መንገደኛው እራሱ ሲያልቅ ነውና፡፡

"ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ!" ~ እመጓ
በዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ

The older you get, the Quiter you become. Life humbles you so deeply as you age. You realize how much non sense you've wasted time on.

Member of

More Clubhouse users