ምን እያነበባችሁ ነው? ምን መጽሐፍ ይዛችኋል?
ሰሞኑን የያዛችሁትን ንባብ፣ አንብባችሁ ሰው ሁሉ ቢያነበው ብላችሁ የጓጓችሁለትን፣ ከውስጣችሁ አልወጣ ብሎ ለሰው ማውራት የምትሹት ኮርኳሪ የንባብ ሀሳባችሁን ብቻ ምን አለፋችሁ የንባብ እና ጽሑፍ ወሬ ሁሉ በዚህ ክፍል እናወጋለን።
ዳዊት ጥበቡም በቋሚ አምዳችን የጀመርነውን አራተኛ መጽሐፍ የተመረጡ ምዕራፎችን ከ"How to Do the work" መጽሐፍ የድምፅ ቅጂ በማጫወት ለውይይት ይጋብዘናል።
በማክሰኞ ምሽት መጽሐፍ ከሚሰጡን ጸሐፍት አንዳቸውን አልያም ከመጽሐፎቻችን ጋር በአንድም በሌላም ሥራ እና ሕይወታቸው የተቆራኙ ቤተሰቦቻችንን ወደ ቤታችን በመጋበዝ የጻፉትን ብሎም ያነበቡትን እናወያያለን።
ዝለቁ እና እንወዳጅ።
በቴሌግራም መጻፍ ብትወዱ
https://t.me/ejachihu
ደምባችን!: ሁሉም ቤተሰብ ነው። የምታነቡትን ይዛችሁ ኑ፤ አዋሩን። የወደዳችሁትን እና ያስከፋችሁን አውሩን።
አታነቡም? ምንም ሀሳብ አይግባችሁ፤ ያነበቡት ያዋሯችኋል።
አሳውቁን!: ጽንፍ ረግጧል ብላችሁ የምታስቡት ሀሳብ ያለው ንባብ ይዛችሁ ከሆነ በትህትና ግለጹልን፤ ለእናንተ ረብ ያለው ከሆነ ምን ገዶን!
አጋሩን!: የወደዳችሁትን መጽሐፍ፣ ያገኛችሁትን አዲስ መረዳት ብሎም ኮርኳሪ የምትሉትን አንቀጽ አጋሩን!
Day | Members | Gain | % Gain |
---|---|---|---|
June 08, 2024 | 1,672 | +20 | +1.3% |
March 11, 2024 | 1,652 | +10 | +0.7% |
January 21, 2024 | 1,642 | +13 | +0.8% |
December 07, 2023 | 1,629 | +15 | +1.0% |
October 31, 2023 | 1,614 | +21 | +1.4% |
September 30, 2023 | 1,593 | +56 | +3.7% |
September 01, 2023 | 1,537 | +29 | +2.0% |
August 03, 2023 | 1,508 | +47 | +3.3% |
July 03, 2023 | 1,461 | +84 | +6.2% |
April 07, 2023 | 1,377 | -1 | -0.1% |